በፈረንሳይ የተስፋፋውን ሰደድ እሳት በተመለከተ ፕሬዝዳንቱ አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ ጠሩ

በፈረንሳይ እና ስፔን በተስፋፋው ሰደድ እሳት ምክንያት ከ330,000 በላይ ሰዎች መኖሪያቸውን ለቅቀው እንዲወጡ ተደርጓል

የፎቶው ባለመብት, EPA

የምስሉ መግለጫ, በፈረንሳይ እና ስፔን በተስፋፋው ሰደድ እሳት ምክንያት ከ330,000 በላይ ሰዎች መኖሪያቸውን ለቅቀው እንዲወጡ ተደርጓል
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ

በደቡብ ምዕራብ ፈረንሳይ ቦርዴዩክስ ግዛት የተስፋፋውን ሰደድ እሳት በተመለከተ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ ሊያደርጉ ነው።

የድንገተኛ ጊዜ አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባው ዛሬ ሰኞ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

በሙቀት ወጀብ ምክንያት ሰደድ እሳቱ እየተስፋፋ ይገኛል። የቦርዴዩክስ ግዛት ከንቲባ ቶማስ ካዜንቪ እንደተናገሩት ሰደድ እሳቱ 15 ኪሎሜትር ይሸፍናል።

በፈረንሳይ እና ስፔን በተስፋፋው ሰደድ እሳት ምክንያት ከ330,000 በላይ ሰዎች መኖሪያቸውን ለቅቀው እንዲወጡ ተደርጓል።

ከንቲባው እንዳሉት 850,000 የሚደርሱትን የግዛቱን ነዋሪዎች ለማስወጣት ዕቅድ የላቸውም።

ባለፈው ሳምንት ፈረንሳይ እና ስፔንን ጨምሮ በአውሮፓ አገራት ሰደድ እሳት ተስፋፍቷል።

ማክኖን ቅዳሜ ባደረጉት ንግግር ፈረንሳይን "መልሰው እንደሚገነቡ" ገልጸዋል።

"አስፈላጊ እስከሆነበት ጊዜ ድረስ" መንግሥታቸው ሥራውን እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

ከቦርዴዩክስ ግዛት አዋሳኝ ቦታዎች በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲወጡ ተደርጓል።

የፈረንሳይ የአገር ውስጥ ሚኒስትር ላውረንት ኑኔዝ ሁኔታው "በጣም አስጊ" እንደሆነ እና ሰደድ እሳቱ "በፍጥነት" ወደ ከተማው እየተስፋፋ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የፈረንሳይ የአየር ሁኔታ ትንበያ እንደሚያሳየው ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ ሙቀቱ እስከ 40 ዲግሪሴንቶ ግሬድ ሊደርስ ይችላል።

በሙቀት ወጀብ ምክንያት ሰደድ እሳቱ እየተስፋፋ ይገኛል

የፎቶው ባለመብት, Jose Jordan/AFP via Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በሙቀት ወጀብ ምክንያት ሰደድ እሳቱ እየተስፋፋ ይገኛል

በጊሮንድ ግዛት የተነሳው ሰደድ እሳት በነፋስ እና ነጎድጓድ ምክንያት ባልተጠበቀ ሁኔታ እየተስፋፋ ይገኛል።

ብሔራዊ የእሳት አደጋ መከላከያ ቃል አቀባይ ኤሪክ ብሮካርዲ "እሳቱ እንዴት እንደሚስፋፋ አናውቅም፤ አቅጣጫውን በተደጋጋሚ እየለወጠ ነው፤ ስለዚህም በቀጥታ ለማጥፋት መሞከር አንችልም" ሲሉ ተናግረዋል።

ሰደድ እሳቱን መቆጣጠር የሚቻለው "በተከታታይ ለሦስት ቀናት ከፍተኛ ዝናብ ከጣለ" እንደሆነ ተናግረዋል።

ሌላኛው አማራጭ ሰደድ እሳቱ ወደ ባሕር አቅጣጫ ሄዶ እንዲጠፋ ማድረግ ነው።

በደቡብ ምዕራብ ፈረንሳይ ሰደድ እሳቱ ወደ 42,000 ሄክታር አውድሟል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ የከፋው ሰደድ እሳት ነው ተብሏል።

ዘንድሮ በመላው ፈረንሳይ ወደ 98,000 ሄክታር ወድሟል።

እስካሁን ድረስ ከ220,000 በላይ ሰዎች ለቅቀው እንዲወጡ ተደርጓል።

ሰደድ እሳቱን መቆጣጠር የሚቻለው "በተከታታይ ለሦስት ቀናት ከፍተኛ ዝናብ ከጣለ" እንደሆነ ተገልጿል

የፎቶው ባለመብት, Lorena Sopena Lopez/Anadolu via Getty Image

የምስሉ መግለጫ, ሰደድ እሳቱን መቆጣጠር የሚቻለው "በተከታታይ ለሦስት ቀናት ከፍተኛ ዝናብ ከጣለ" እንደሆነ ተገልጿል
Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

በስፔን ትናንት እሑድ የተነሳውን አዲስ ሰደድ እሳት ለማስቆም የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች እየተረባበሩ ነው።

በምሥራቃዊቷ የወደብ ከተማ ቫሌንስያ በተነሳው ሰደድ እሳት ምክንያት ወደ 15,000 ሰዎች አካባቢውን ለቅቀው ወጥተዋል።

የማዕከላዊው መንግሥት ተወካይ ፒላር በርናቢ ሰደድ እሳቱ "በጣም ከፍተኛ" እንደሆነ እና የአየር ሁኔታውም እንደተባባሰ እንደሚሄድ ገልጸዋል።

የስፔን የአገር ውስጥ ሚኒስትር ፈርናንዶ ግራንድ-ማርላስካ በቫለንሲያ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ዛሬ ሰኞ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሰደድ እሳቱ ቀስ በቀስ እየተስፋፋ መሄዱን ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ከማድሪድ በስተምዕራብ የሚገኘውን አቪላ ሲጎበኙ "ከፊታችን ከባድ ሰዓታት ይጠብቁናል" ብለዋል።

በድንገተኛ የአየር ንብረት ለውጥ ጫና ምክንያት "የድንገተኛ ጊዜ አዋጅ" እንዲደነገግ ጠይቀዋል።

የአገሪቱ ንጉሥ ፊሊፔ አራተኛ ሰደድ እሳቱ በተፈጥሮ ሃብት ላይ "ሊገመት የማይችል ጉዳት" አስከትሏል ብለዋል።

የስፔን ኢኮሎጂ ሚኒስትር ሳራ አጌሰን እንደተናገሩት፤ ወደ 77,000 ሄክታር ውድመት ደርሶበታል።

በአቪላ ግዛት የተነሳው ሰደድ እሳት በአገሪቱ ታሪክ ሰፊው መሆኑን ገልጸዋል።

ከአካባቢው ለቅቀው ከወጡ መካከል አንዷ የሆኑት የ50 ዓመቷ ኦልጋ ኮንጋቻ ቤታቸውን ጥለው እንዲወጡ ሲነገራቸው "መደናገጣቸውን" ተናግረዋል።

"ማልቀስ ይኖርብኝ እንደሆነ አላውቅም። በጣም መጥፎ ስሜት ነው የተሰማኝ" ብለዋል።

ቤታቸው በአመድ ተሸፍኖ፤ አውራ ጎዳናዎች ሰው አልባ ሆነው መመልከታቸው አሳሰዝኗቸዋል።

ንፋስ ሰደድ እሳቱን ወደ መዲናዋ ማድሪድ እየገፋው መሆኑ ተገልጿል።

ማድሪድ እና አቪላ ዙሪያ ያሉ ከ90,000 በላይ ነዋሪዎች ቤታቸውን ጥለው ወጥተዋል።